የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ምዕራብ ቻይና ቸንዱ ከተማ የካርጎ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ከሁለት ሳምንት በፊት ነው።
ወደ ቻይና የምናደርገው የካርጎ በረራ በአፍሪካ እና በቻይና መካከል ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ እና በቻይና መካከልም ጭምር ነው። ስለዚህ በቻይና ትልቅ የካርጎ ኦፕሬሽን አለን። ምርቶቻቸውን ወደ አፍሪካ፣ አውሮፓና ሌሎች የዓለም ክፍሎች ለመላክ ከቻይና ነጋዴዎች ጋር ስንሠራ ቆይተናል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚው።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አምስት የቻይና መዳረሻዎች ማለትም ቤጂንግ፣ ጓንጆ፣ ሻንጋይ፣ ቸንዱ እና ሆንግ ኮንግ በድምሩ 52 ሳምንታዊ በረራዎች – 28 የመንገደኞች እና 24 የካርጎ በረራዎች በረራ ያደርጋል።
“እኔ እስከማውቀው ድረስ በኢትዮጵያ እና በተቀረው አፍሪካ ውስጥ ኢንቨስት የሚያደርጉ የቻይና ኩባንያዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።” አየር መንገዱ ወደ ቻይና እና አፍሪካ ለሚበሩ ነጋዴዎች አገልግሎት መስጠት እና የንግድ ልውውጥን ለማሳለጥ እንደ ማነቃቂያ ሆኖ መስራቱ ትልቅ እድል ነው።” ሲሉ ተናግረዋል አቶ መስፍን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደገለፁት ድርጅታቸው የቻይናን ህዝብ ለታላቁ አፍሪካ ገበያ ያለውን አገልግሎት እና ተደራሽነት ያሳድጋል። “አየር መንገዱ በቻይና እና አፍሪካ መካከል ባለው ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለን እናምናለን።”
ምንጭ፡- Xinhua