የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሌዥ ከተማ ከቀዳሚየጭነት አየር መንገዶች ተርታ መሰለፉን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎት በቤልጂየም የሌዥ ከተማ ቀዳሚ ከሆኑ የጭነት አየር መንገዶች ተርታ መሰለፉን አስታወቀ።

አየር መንገዱ በፈረንጆቹ 2023 ከ160 ሺህ ቶን በላይ ጭነት ከሌዥ ከተማ ወደ ተለያዩ አኅጉራት በብቃት ማመላለሱን አየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።

በዚህም መሠረት ወደ አፍሪካ፣ ኤስያ፣ አውሮፓ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ ሀገራት በትጋት በማመላለስ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *