570 ስታርት አፖች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይ በሣይንስ ሙዚየም ተከፈተ።
ለሦስት ሣምንታት በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይ÷ የመጀመሪያ ደረጃ፣ የመጀመሪያ ደረጃን የተሻገሩ እና ወደገበያ የመቀላቀል ደረጃ ላይ የደረሱ ስታርት አፖች ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል።
የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃያት ካሚል፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው ዐውደ-ርዩ የተከፈተው።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ