የቢትኮይን ዋጋ በ2025 ወደ 150 ሺህ ዶላር ያድጋል ተብሏል
የአንድ ቢትኮይን ዋጋ 106 ሺህ ዶላር ደረሰ።
ከአንድ ዓመት በፊት የአንድ ቢትኮይን ዋጋ 44 ሺህ ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ወደ 106 ሺህ ዶላር ከፍ ብሏል።
ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ተደርገው መመረጣቸውን ተከትሎ የምናባዊ ገንዘብ ወይም ክሪፕቶከረንሲ ዋጋ እየጨመረ ይገኛል።
ዶናልድ ትራምፕ የቢትኮይን ደጋፊ መሆናቸውን በይፋ ከተናገሩ በኋላ የቢትኮይን ዋጋ በፍጥነት እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።
ከአንድ ወር በፊት በተካሄደው የአሜሪካ ምርጫ ዋዜማ ዕለት አንድ ቢትኮይን በ 68 ሺህ ዶላር ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ አንድ ቢትኮይን በ106 ሺህ ዶላር ደርሷል ሲል ብሉምበርግ ዘግቧል።
ዶናልድ ትራምፕ ከተመረጡ በኋላ የቢትኮይን ዋጋ በ50 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ሀገራቸው የነዳጅ መጠባበቂያ እንዳላት ሁሉ የቢትኮይን መጠባበቂያም እንዲኖር አደርጋለሁ ብለዋል።
የአንድ ቢትኮይን ዋጋ አንድ ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ተባለ
እንደ ክሪፕቶ ከረንሲ ባለሙያዎች መረጃ ከሆነ የያዝነው የፈረንጆቹ 2024 ከመጠኛቀቁ በፊት የቢትኮይን ዋጋ 120 ሺህ ዶላር ይደርሳል።
እንዲሁም በ2025 ደግሞ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ወደ 150 ሺህ ዶላር ያድጋል የጠባለ ሲሆን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ወደ አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደሚያድግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ከአንድ ወር በኋላ በይፋ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ስራ የሚጀምሩት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ የፔይፓል ክፍያ ስራ አስኪያጅ እና የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት ደጋፊ የሆኑት ዴቪድ ሳክስን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ክሪፕቶ ጉዳዮች ሀላፊ አድርገው መሾማቸው ይታወሳል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ