የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስቴንስን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም፣ የኖርዌይ ባለሃብቶች የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች በጥልቀት እንዲቃኙ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
በተጨማሪም ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሳተፉ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።
በኢትዮጰያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማርተው ለሚገኙ ባለሃብቶች የጋራ የድጋፍ እና ክትትል ስራ ለመስራት የሚያስችል ምክክር መደረጉም ተጠቁሟል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን