የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።
የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
ቀደም ሲል የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ?
- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም ነው።
ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር