የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ የ “N7 ፒክ አፕ” ሞዴል ተሽከርካሪ ለገበያ ሊያቀርብ ነው

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የ “N7 ፒክ አፕ” ሞዴል ተሽከርካሪ ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑን አስታወቀ።

ኢንዱስትሪው በተያዘው የበጀት ዓመት 250 የ “N7 ፒክ አፕ” ሞዴል ተሽከርካሪ ለማምረት አቅዶ እየሠራ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።

ከዚህ ዕቅድ ውስጥ በመጀመሪያ ዙር 39 የ “N7 ፒክ አፕ” ገጣጥሞ ለደንበኞቹ ለማቅረብ የምርት ግብዓት ማስገባቱን ከግሩፑ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

አዲሱ የ “N7 ፒክ አፕ” ሞዴል ተሽከርካሪ የዘመኑ የመጨረሻ ምርት እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ያሟላ መሆኑም ተገልጿል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *