የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት እና ጉድ ኔበርስ ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ ለመስራት ተስማሙ
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ እንዳመለከቱት ጉድ ኔበርስ ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት እየተከናወኑ ያሉትን በርካታ የልማት ስራዎች ለመደገፍ እንዲሁም በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
በውይይታቸውም ቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት እና ጉድ ኔበርስ ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
ጉድ ኔበርስ ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት የተመሰረተበት ዋናው መቀመጫውን ኮሪያ ሪፐብሊክ ያደረገ ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑም በመረጃው ተመላክቷል።
ምንጭ፦ ኢዜአ