የመስከረም 7 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል?

የግል ባንኮች አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በሃዋላ የሚላክ 1 ዶላርን እስከ 126 ብር እየመነዘሩ ነው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ1 ዶላር ላይ ከ4 ብር በላይ ጭማሪ በማድረግ በ112 ብር ገዝቶ በ124 ብር እየሸጠ ነው

ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የ2017 አዲስ ዓመት አስመልክቶም ባንኮች በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያውን በባንኮች አማካኝነት ገንዘብ እንዲልኩ የሚያበረርታታ ተመን እያወጡ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል የሚላክን ገንዘብ ከባንኩ ለሚቀበሉ ደንበኞቹ ተጨማሪ የ6.82 በመቶ የበዓል ስጦታ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ባንኩ ዛሬ መስከረም 7 2017 ዓ.ም መደበኛ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ትናንት ካወጣው ዋጋ ላይ ከ4 ብር በላ ጭመሪ በማድረግ፤ 1 ዶላርን በ112.3957 ብር እየገዛ በ124.7592 ብር እየሸጠ ይገኛል።

እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ የሚላክን አንድ የአሜሪካ ዶላር በ125 ብር እንደሚመነዝር ያስታወቀው ንብ ባንክም መደበኛውን (እለታዊ የምንዛሬ ተመን) ይፋ አድርጓል።

በዚህም ባንኩ ከትናንት የምንዛሬ ዋጋው ላይ መጠነኛ ጭማሪ በማድረግ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ108.0994 ብር እየገዛ በ121.0714 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጿል።

ፀደይ ባንክ ዛሬ በለቀቀው የመስከረም 7 2017 ዓ.ም እለታዊ የውጭ ምንዛሬ የዋ ዝርዝር አንድ የአሜሪካ ዶላር በ110.1796 እንደሚገዛ እና መሸጫውን ዋጋውን ደግሞ 123.4011 ማድረሱን ኣሳተውቋል።

ዳሸን ባንክ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የምንዛሬ ዋጋ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህም በሃዋላ የሚላክ 1 ዶላርን ከመደበኛው የምንዛሬ ዋጋ ላይ እስከ 16 በመቶ ጉርሻ እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወቃል።

ባንኩ በመደበኛ የምንዛሬ ዋጋው ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ108.0703 ብር እየገዛ በ121.5791 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ ያደረገው።

ኦሮሚያ ባንክም በዓልን ምክንያት በማድረግ ከውጪ በሃዋላ የተላከ አንድ የአሜሪካ ዶላርን ከእለታዊ ተመን በተጨማሪ 17 በመቶ ጉርሻ እንደሚሰጥ እና በዚህም 1 ዶላርን በ126+ ብር እንደሚመነዝር ማስታወቁ ይታወሳል።

ባንኩ የዛሬ የመስከረም 6 2017 መደበኛ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ 1 የአሜሪካ ዶላር በ108.0920 ብር እየገዛ በ122.1440 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የጠቆመው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *