የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ጥሪ አቀረቡ።
በህንድ ሙምባይ ከተማ የእስያ አፍሪካ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው ስድስተኛው ዓለም አቀፍ የንግድ አመራሮች ፎረም ተካሂዷል።
አምባሳደሩ በፎረሙ ላይ እንደገለጹት÷ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የግብርና፣ የማምረቻ፣ የማዕድን፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ቱሪዝም ዘርፎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ናቸው።
በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ከተሰማሩ ኩባንያዎች መካከል የህንድ ኩባያዎች በሁለተኛ ደረጃ እንደሚገኙም መገለጹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ