የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች በመሰማራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍሰሃ ሻወል ጥሪ አቀረቡ።
አምባሳደሩ በህንድ በተካሄደው ዓለም አቀፉ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ማህበር (WASME) ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል።
በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግርም፥ በኢትዮጵያ ምቹ የሆኑ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዳሉ አብራርተዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሃብቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ እድሎች መመቻቸታቸውን ተናግረዋል።
በተለይም በግብርና፣ማኑፋክቸሪንግ፣አይሲቲ፣ ማዕድንና ቱሪዝም ዘርፎች ገና ያልተነኩ እምቅ ሃብቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
በመሆኑም የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች በመሰማራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ እና ህንድ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረና አሁንም በተጠናከረ መልኩ የቀጠለ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ምንጭ፦ ኢዜአ