
የህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መስክ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ።
በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ሞላልኝ አስፋው ከህንዱ ፒኤችዲ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና ኬኤልጂ ግሩፕ ኦፍ ኢንዱስትሪስ ከተሰኘው አምራች ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሽሪ ሄርማንት ጃን ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ የኢትዮጵያ እና ህንድ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው።
አምባሳደር ሞላልኝ የኢትዮጵያን ብዝሃ የኢንቨስትመንት እድሎች አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ያሉ አማራጮችን እንዲቃኝ ጥሪ አቅርበዋል።
ሽሪ ሄርማንት ጃን በምክር ቤቱ ስር ያሉ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው እ.አ.አ ጁን 2025 የንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።
ከ130 ሺህ በላይ አባላት ያሉት ፒኤችዲ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የህንድ ላኪዎችን የሚወክል ግዙፍ ተቋም መሆኑን በኒው ዴልሂ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
ኬኤልጂ ግሩፕ ኦፍ ኢንዱስትሪስ በህንድ እና እስያ ግዙፍ የፕላስቲክ እና የፕላስቲክ ውጤቶች አምራች ኩባንያ ነው።
ምንጭ፦ ኤፍ.ኤም.ሲ