ኩዌት፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እ ቦትስዋና ዝቅተኛ የብድር ጫና ካለባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
የሩቅ ምስራቋ ጃፓን ከዓመታዊ ትርፏ በላይ የሆነ የብድር ጫና ያለባት ቀዳሚዋ ሀገር ናት
ዝቅተኛ የብድር ጨና ያለባቸው ዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
እንደ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም አይኤምኤፍ ሪፖርት ከሆነ ኩዌት ያለባት ብድር ከዓመታዊ ኢኮኖሚዋ ወይም ጂዲፒ 11 በመቶ ያህል ብቻ ነው
አፍሪካዊቷ የማዕድናት ሀብታም ሀገር ዲሞክራቲክ ኮንጎ ዝቅተኛ የብድር ጫና ካለባቸው ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ስትሆን ያለባት ብድር መጠን ከዓመታዊ እድገቷ የ15 በመቶ ድርሻ አለው።
አዛርባጂያ፣ ቦትስዋና እና ኢስቶኒያም አነስተኛ የብድር ጫና ካለባቸው ሀገራት ተርታ የተቀመጡ ሀገራት እንደሆኑ የዚሁ ተቋም ሪፖርት ያስረዳል።
ጃፓን ከፍተኛ የብድር ጫና ካለባቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ስትሆን የብድር መጠኗ ከዓመታዊ እድገቷ ሁለት እጥፍ ድርሻ አለው ተብሏል።