
ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።
የሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገሙ ነው።
በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ፤ በኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ ለ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ተገልጋዮች አገልግሎት መሰጠቱን እና 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የድረ-ፍቃድ ኢንስፔክሽን መከናወኑን ገልጸዋል።
374 ተጨማሪ የሰንበት ገበያዎች ተቋቁመዋል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።
ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱን ጠቅሰው፤ ይህም በሀገሪቱ ወጪ ንግድ ታሪክ ከፍተኛው ነው ብለዋል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ኤም.ሲ