ከወርቅ ወጪ ንግድ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

 ባለፉት ሥድስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

ኢትዮጵያ ባላት የተለያየ መልክዓ ምድር እና ምቹ የአየር ንብረት ብዝሃ-ምርቶችን አምርታ ለዓለም የማቅረብ ዕምቅ አቅም እንዳላት ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል።

ለአብነትም “ማዕድን እንደማሳያ ብንወስድ ባለፉት ስድስት ወራት ከወርቅ ብቻ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ አግኝተናል” ብለዋል።

አቅማችንን አጎልብተን ወደ ገቢራዊ ውጤት መቀየርና በልኩ ማስተዋወቅ ያስፈልጋል ሲሉም ገልጸዋል።

የቡና፣ የጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ ሰብሎች፣ ቅመማቅመም፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ማዕድንና ሌሎች ምርቶቻችንን በጥራት አምርተን በወጪ ንግድ በዓለም ገበያ ያለንን ድርሻ እያሻሻልን ከሄድን ከዘርፉ የምናገኘው ገቢ በብዙ እጥፍ ይጨምራል ብለዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *