ከአሜሪካ ነጻ የንግድ ስምምነት አጎዋ የታገዱ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው? የውጭ ንግድ አፈጻጸማቸውስ ምን ይመስላል?

የአፍሪካ ሀገራት ከቀረጥ ነጻ ምርቶቻቸውን ወደ አሜሪካ እንዲልቁ የሚፈቅደው የአጎዋ ስምምነት 38 ሀገራትን በአባልነት ይዞ የጀመረ ነው

በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ 12 የአፍሪካ ሀገራትን ከዚህ ስምምነት ማስወጣቷ ይታወቃል

የአፍሪካ ሀገራት ወደ አሜሪካ ከቀረጥ ነጻ ምርቶቻቸውን እንዲልኩ የሚፈቅደው የአጎዋ ስምምነት በፈረንጆቹ 2000 የተጀመረ ሲሆን ስምምነቱ እየተራዘመ እዚህ ደርሷል።

38 የሚደርሱ ከሰሀራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት በዚህ ስምምነት በመጠቀም ከ6 ሺህ በላይ ምርቶችን እንዲልኩ ስምምነቱ አድል አመቻችቷል።

በጊዜ ሂደት በስምምነቱ የሚጠቀሙ ሀገራት ቁጥር እየበረከተ ቢመጣም በዚያው ልክ በሰብበአዊ መብት ጥሰት፣ ገበያ መር ኢኮኖሚን ባለመከትል፣ በመፈንቅለ መንግስት እና በተለያዩ ምክንያቶች 12 ሀገራት ከስምምነቱ እንዲወጡ ተደርገው በአሁኑ ወቅት 32 አባል ሀገራትን ይዞ ቀጥሏል፡፡

ይህን ስምምነት ተከትሎ የአፍሪካ ሀገራት ኢንዱስትሪያል ምርቶች መዳረሻ ከሆኑ ሀገራት መካከል አሜሪካ በሶስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች፡፡

በ2001 55 ሚልየን ዶላር ብቻ ግምት ያላቸውን ምርቶች ወደ ዋሽንግተን ስትልክ የነበረችው ኬንያ በ2022 603 ሚልየን ዶላር የአጠቃላይ ለውጭ ገበያ ከምታቀርበው ምርት 67.3 በመቶውን ወደ አሜሪካ አሻግራለች፡፡

 በተመሳሳይ አመት ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የምትልካቸው ምርቶች ዋጋ 29 ሚልየን ዶላር ግምት ያላቸው ሲሆን በ2020 ይህ ቁጥር ወደ 505 ሚልዮን ዶላር ተሻግሯል፡፡

ከአጎዋ የታገዱ እና በስምምነቱ ከፍተኛ ጥቅም ያገኙ የነበሩ ሀገራት እነማን ናቸው?

1. ኢትዮጵያ – በአጠቃላይ ከታገዱት 12 ሀገራት መካከል ከፍተኛ መጠን ያለው ምርት ወደ አሜሪካ በመላክ እና በማስገባት ቀዳሚዋ ነች

• የታገደችበት አመት 2022

• ከአሜሪካ የምታስገባው ምርት 1.1 ቢሊየን ዶላር

• ወደ አሜሪካ የምትልከው ምርት 718 ሚሊየን ዶላር

2. ኡጋንዳ

• የታገደችበት አመት 2024

• ከአሜሪካ የምታስገባው 167 ሚሊየን ዶላር

• ወደ አሜሪካ የምትልከው 174 ሚሊየን ዶላር

3. ጋቦን

• የታገደችበት አመት 2024

• ከአሜሪካ የምታስገባው 133 ሚሊየን ዶላር

• ወደ አሜሪካ የምትልከው 220 ሚሊየን ዶላር

እነዚህ ሀገራት ከአግዋ ከታገዱት ከፍተኛ የውጪ እና ገቢ ምርት ያንቀሳቅሱ የነበሩ ሲሆን ከነዚህ በተጨማሪ ደቡብ ሱዳን፣ ካሜሮን፣ ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ፣ ሞሪታንያ፣ ኒጄር፣ ብሩንዲ እና ማዕከላዊ አፍሪካ በዝርዝር ውስጥ ይገኛሉ።

ለመጨረሻ ጊዜ የተራዘመው የአጎዋ ስምምነት የስራ ጊዜ በመጪው 2025 ይጠናቀቃል።

ምንጭ፦ አል አይን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *