ኤምባሲው በኢትዮጵያ ኢንቨስት የሚያደርጉ የጃፓን ባለሀብቶችን ቁጥር ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ

ተጨማሪ የጃፓን ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ኢንቨስት እንዲያደርጉ በትኩረት እየሠራ መሆኑን በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ጋር የተወያዩት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ፤ የጃፓን ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ኢንቨስት እንዲያደርጉ በትብብር መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለዚህም ኮርፖሬሽኑ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን አቶ አክሊሉ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኮች እያመረቱ የሚገኙ ዓለም ዓቀፍና ሀገር በቀል ኩባንያዎች አሁን ላይ ካላቸው ገበያ በተጨማሪ የጃፓንን ሰፊ የገበያ አቅም መጠቀም በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል።

አምባሳደሩ በበኩላቸው÷ በቅርቡ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፓስፖርትን ጨምሮ ዓለም ዓቀፍ የደኅንነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ምስጢራዊ የሕትመት ውጤቶችን የሚያመርት ቶፓን ግራቪቲ የተሰኘ ግዙፍ የጃፓን ኩባንያ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡን አስታውሰዋል።

ተጨማሪ የጃፓን ባለሀብቶችም በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ኢንቨስት እንዲያደርጉ በትኩረት እየሠራን ነው ማለታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *