አየር መንገዱ ወደ ማካው ከተማ የመጀመሪያ የካርጎ በረራውን አደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይናዋ ማካው ከተማ የመጀመሪያ የካርጎ በረራውን ዛሬ ማለዳ አድርጓል።

አየር መንገዱ በማካው ባስጀመረው የካርጎ አገልግሎት ስነ ስርዓት ላይ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ተገኝተዋል።

አየር መንገዱ በቻይና ያለውን የካርጎ መዳረሻ ወደ 10 ከፍ አድርጓል።

አምባሳደር ተፈራ ደርበው የአገልግሎቱ መጀመር አየር መንገዱ የካርጎ ትስስሩን ለማስፋት እና የዓለም ንግድን ለማሳለጥ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነ መግለጻቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *