የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከተለያዩ የአሜሪካ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የ2024 የዓለም ባንክ እና አይኤም ኤፍ ስብሰባዎች ጎን ለጎን በሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የሚመራው ልዑክ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት አምባሳደር ሞሊ ፊ፣ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክል ሀመር እና የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ግምጃ ቤት ምክትል ፀሐፊ ጄይ ሻምባህ ጋር ተወያይቷል።
ውይይቱ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ እንዲሁም የሀገሪቱን የማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፍ ለማሻሻል በሚደረጉ ማሻሻያዎች ላይ ያተኮረ እንደሆነ መገለጹን በአሜሪካ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ሁለቱ ወገኖች በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ በኩል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚያገግምበትን ሁኔታ ለመፍጠር፣ ሀገራዊ ትስስር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማስፈን በሚያስፈልገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ላይ ተወያይተዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ