ቻይና ፖሊሲዋን ያሻሻለችው ጎብኚዎችን ለመሳብ እንደሆነ አስታውቃለች
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ በዚህ ፖሊሲ የተፈቀደለት ሀገር የለም
ቻይና 54 ሀገራት ያለ ቪዛ እንዲጎበኟት ፈቀደች።
የሩቅ ምስራቋ ሀገር ቻይና የጎብኚዎችን ቁጥር ለመሳብ የነበራትን የቱሪዝም ፖሊሲ አሻሽላለች።
የዓለማችን ሁለተኛ ልዕለ ሀያል ሀገር የሖነችው ቻይና 54 የዓለማችን ሀገራት ያለ ቪዛ እንዲጎበኟት የፈቀደች ሲሆን ያለ ቪዛ ወደ ግዛቷ እንዲገቡ፣ ለ10 ቀናት እንዲቆዩም ፈቅዳለች።
ጎብኚዎች በአየር፣ በወደቦች እና በድንበሮቿ በኩል ወደ 24 ግዛቶች ያለ ቪዛ እንዲገቡ የፈቀደች ሲሆን ጎብኚዎች የቆይታ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙ የሚያደርግም አሰራር መዘርገቷን አስታውቃለች።
ያለ ቪዛ እንዲጎበኟት ከተፈቀደላቸው ዜጎች መካከል የአውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ ዋነኞቹ ሲሆን ከደቡብ አሜሪካ ደግሞ ሜክሲኮ፣ ብራዚል እና ቺሊ ዋነኞቹ ናቸው።
ከአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሁሉም የአህጉሪቱ ሀገራት ያለ ቪዛ እንዲገቡ ከተፈቀደላቸው ሀገራት መካከል ሳይካተቱ ቀርተዋል።
ስለ ሸንገን ቪዛ ማወቅ ያሉብን አዳዲስ ውሳኔዎች ምን ምን ናቸው?
ጎብኚዎች በተለይም የቻይና ባህላዊ እና ታሪካዊ ቦታዎችን እንዲጎበኙ፣ የቢዝነስ እና ተያያዥ ስብሰባዎችን ለማድረግ ይበረታታሉም ተብሏል።
ሀገሪቱ እስከ ታህሳስ 2025 ድረስ የ38 ሀገራት ዜጎች ለአንድ ወር ያህል ያለ ቪዛ ዜጎች በቻይና እንዲቆዩ የሚፈቅድ አሰራር እንዳላትም አስታውቃለች።
ይሁንና ከቢዝነስ፣ ጉብኝት፣ ቤተሰብ ጥየቃ እና ወደ ሌላ ሀገር ለማምራት የሚፈልጉ ተጓዦች ካልሆነ በስተቀር ለሌሎች ጉዳዮች የነጻ ቪዛ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን አይችሉም ተብሏል።
ምንጭ፦ አል.አይን