ባለፉት 10 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበ የቡና ምርት 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ 

ባለፉት 10 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበ 210 ሺህ ቶን ቡና 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ገለጸ።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ የምታቀርበው የቡና ምርት በየዓመቱ እየጨመረ ነው።

በተያዘው በጀት ዓመት አሥር ወራትም 210 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ መቅረቡን ገልጸዋል።

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ እንዳለው ጠቁመው በዚህም 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ነው ያስረዱት።

ኢትዮጵያ ከ50 እስከ 60 ለሚሆኑ ሀገራት ቡና የምትልክ መሆኑን ገልጸው የኢትዮጵያ ቡና መዳረሻ ሀገራትን ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም በተለያዩ ሀገራት የቡና አውደ ርዕዮችን በማዘጋጀትና ሌሎች ተግባራትን በማድረግ ቡናን የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከቡና ንግድ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለማስቀረትና የዘርፉን የውጭ ንግድ አፈጻጸም ለማሳደግ ዘመናዊ አሰራር ገቢራዊ መደረጉን ጠቁመዋል።

አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ቢልጂየም፣ጀርመንና ሳኡዲ አረብያ የኢትዮጵያ ቡና በብዛት ወደ ሀገራቸው የሚያስገቡና የሚጠቀሙ ሀገራት መሆናቸው ተገልጿል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *