የኢራን ሪያል ቀዳሚ ሲሆን፤ 1 የዶላር በ42 ሺህ 45 የሀገሪቱ ገንዘብ (ሪያል) ይመነዘራል
በፈረንጆቹ 2024 ከዶላር አንጻር ገንዘባቸው ደካማ የሆነ 10 የዓለም ሀገራት ከሰሞኑ ይፋ ተደርገዋል።
የአንድ ሀገር ገንዘብ በሌላ ሀገር ገንዘብ ሲመነዘር ያለው ዋጋ ጥንካሬውን እን ድክመቱን ያሳያል የተባለ ሲሆን፤ ኤፍ.ኤክስ.ኤስ.ኤስ.አይ ድረ ገጽ ከሰሞኑ ከከዶላር አንጻር ገንዘባቸው ደካማ የሆነ 10 የዓለም ሀገራትን ይፋ አድርጓል።
ከዓለም ከዶላር አንጻር ደካማ ገንዘብ ያላት ቀዳሚ ሀገር ኢራን ነች የተባለ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ42 ሺህ 45 የሀገሪቱ ገንዘብ (ሪያል) ይመነዘራል።
የቬትናም ገንዘብም ከዶላር አንጻር ደካማ ከሚባሉት ውስጥ 2ኛ ደረጃ ለይ የተቀመጠ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ24 ሺህ 469 የቬትናም ገንዘብ (ዶንግ) ይመነዘራል።
የስራሊዮን ገንዘብም ከዶላር አንጻር ደካማ ከሚባሉት ውስጥ 3ኛ ደረጃ ለይ የተቀመጠ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ22 ሺህ 418 ሴራሊዮን ገንዘብ (ሊዮን) ይመነዘራል።
4ኛ ደረጃ ላይ የተመቀጠው የላኦ ወይም ላኦቲን ኪፕ ገንዘብ ሲሆን፤ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ20 ሺህ 594 ላኦቲን ኪፕእየመተመነዘረ መሆኑ ነው የተነገረው።
የኢንዶኔዢያን ሩፖያህ ደግሞ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል የተባለ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ሶላር በ15 ሺህ 619 የኢንዶኔዢያን ሩፒያህ ይመነዘራል ነው የተባለው።
6ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የኡዝቤኪስታን ገንዘብ ነው፤ በዚህም 1 የአሜሪካ ዶላር በ12 ሺህ 335 የኡዝቤክ ሰም ነው የሚመነዘረው ይላል መረጃው።
የጊኒ ገንዘብም በ7ኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ8 ሺህ 583 የሀገሪቱ ገንዘብ (ጊኒ ፍንክ እንደሚመነዝርም ተመልክቷል።
የፓራጓይ ገንዘብ 8ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ7 ሺህ 280 የፓራጓይ ጓራኒ እንደሚመነዘር ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።
9ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የካምቦዲያ ገንዘብ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ4 ሺህ 86 የካምቦዲያን ሬይል እንደሚመነዘርም ተነግሯል።
የኮሎምቢያ ገንዘብ 10ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፤ በዚህም 1 የአሜሪካ ዶላር በ3 ሺህ 915 የኮሎምቢያን ፔሶ እንደሚመነዘርም ነው የተገለጸው።