በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ከኳታር ባለሃብቶች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኢትዮጵያን ወጪ ምርቶች በመቀበል እና በሀገራችን መዋዕለ-ነዋያቸውን ኢንቨስት በማድረግ ረገድ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ስጋቶችን እንዲሁም ስላለው ምቹ ሁኔታ ከባለሃብቶቹ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል።
በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ስለሚኖረው ትብብር እና የንግድ ልውውጥ ዙሪያ ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውንም አመላክተዋል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ