በኢትዮጵያና ኮሪያ ሪፐብሊክ መካከል በቀጣይ አራት ዓመታት ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የ1 ቢሊየን ዶላር የፋይናንስ ማዕቀፍ ስምምነት ተፈረመ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኮሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት በፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ይኦል አቀባበል ተደረጎላቸዋል።
ሁለቱ ወገኖችና የልዑካን ቡድኖቻቸው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ፌዴራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እና በደቡብ ኮሪያ ፀረ ሙስና እና ሲቪል መብቶች ኮሚሽን መካከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
በሁለትዮሽ ውይይቱ አማካኝነት በቀጣይ አራት ዓመታት ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የ1 ቢሊየን ዶላር የፋይናንስ ማዕቀፍ ስምምነትም በዛሬው ዕለት ተፈርሟል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ