በአፍሪካ ከፍተኛ የወርቅ ተቀማጭ ያላቸው 10 ሀገራት

የዋጋ ግሽበትን ተከትሎ ሀገራት በግምዣ ቤቶቻቸው ከፍተኛ የመግዛት አቅም ያለቸውን የውጭ ገንዘቦችና ወርቅ ያስቀምጣሉ

በአፍሪካም እያጋጠመ ያለውን የገንዘብ መግዛት አቅም መዳከምን ለመቋቋም ወርቅ በግምዣ ቤቶች ይቀመጣል

በአለም አቀፍ ደረጃ ተለዋዋጭ የሆነው ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ የሚፈጥረው የዋጋ ግሽበት ኢኮኖሚያቸው ባልዳበረ ሀገራት ላይ የሚያሳደረው ተጽእኖ ከፍ ያለ ነው።

 በተለይ እንደ አሜሪካን ዶላር አይነት ካሉ አለም አቀፍ የመገበያያ ገንዘቦች አንጻር መወዳደደር የማይችለው ገንዘባቸው የሚፈጥረው ኢኮኖሚያዊ ጫናን ለመከላከል ሀገራት ወርቅን የመሳሰሉ ተፈላጊ ማዕድናትን በግምዣ ቤቶች ያስቀመጣሉ።

ከፍተኛ የማዕድን ክምችት እንዳላት በሚነገርላት አፍሪካ በሜትሪክ ቶን የሚመዝን ወርቅ በግምዣ ቤቶች ውስጥ ይገኛል።

 የወርቅ ክምችቱ በክፉ ጊዜ ሀገራት ሽጠው ኢኮኖሚያቸውን የሚደጉሙበት የውጭ ምንዛሬ ማግኛ መንገድ ነው።

በዚህ ረገድ ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ 175 ሜትሪክ ቶን የወርቅ ተቀማጭ በመያዝ በአፍሪካ ቀዳሚዋ ስትሆን ደቡብ አፍሪካ በ125 ሜትሪክ ቶን በቅርብ ርቀት ትከተላለች።

ምስል፦ አል አይን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *