የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር እስከ 124 ብር መግዣ እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ከ26 ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሎ 1 ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ ከ26 ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ የታህሳስ 10 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ከሶስት ሳምንት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.6490 ብር ገዝቶ በ127.1420 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጸደይ ባንክም በውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ ዶላር በ124.7404 ብር ገዝቶ በ127.2353 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ነው በእለታዊ ተመኑ ላይ ያመላከተው።
ምንጭ፦አል.አይን