የሶማሌ ክልል ገቢዎች ቢሮ ባለፉት 11 ወራት 12 ነጥብ 28 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አስታውቋል።
ቢሮው ለታክስ አምባሳደሮች ባዘጋጀው የእውቅና መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን እንዳሉት÷ለተመዘገበው የላቀ ውጤት የታማኝ ግብር ከፋዮች ሚና ከፍተኛ ነው።
ዕውቅና የተሰጣቸው የክልሉ የታክስ አምባሳደሮች በቀጣይ በክልሉ የታቀደው ዕቅድ ስኬታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።
በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ግብርን በአግባቡ መክፈልና መሰብሰብ ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ መሃመድ አብዲ ኡመር በበኩላቸው÷ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ለማሻሻልና ለማዘመን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
በ2016 የበጀት ዓመት 16 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ በ11 ወራት 12 ነጥብ 28 ቢሊየን ብር መሰብሰብ እንደተቻለ መግለጻቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ