በአዲስ አበባ ከተማ ህግና አሰራርን የማይከተሉ የመንደር ንግዱን ማህበረሰብ መቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ።
መመሪያው በከተማ አስተዳደሩ የገቢ አሰባሰብ ላይ የሚያስቸግሩ ህገወጦችን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሀላፊ አቶ ቢንያም ምክሩ ተናግረዋል።
በመንደር ንግድ ቁጥጥር አሰራር ስርዓት መመሪያ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በዚህ መመሪያ ላይ ባተኮረው የውይይት መድረክ የንግዱ ማህበረሰብ የሸማች ማህበራትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል።
በመንደር ንግድ ላይ ተገቢውን አካሄድ ለማስፈን የመንደር የንግድ አሰራር ስርዓት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱም ተመላክቷል።
በተጨማሪም መመሪያው በአዲስ አበባ የንግዱ ማህበረሰብ ከንግድ ቁጥጥር ተግባራት ጋር በተያያዘ ከሚደርሱበት ወከባዎች በማላቀቅ በተረጋጋ መንፈስ ስራውን ማከናወን የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ