በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ከ160 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስመዘገቡ ባለሃብቶች የግንባታና የማሽን ተከላ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ

በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ከ160 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስመዘገቡ ባለሃብቶች የግንባታና የማሽን ተከላ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን እንቅስቃሴ የጀመሩት ስድስት የሃገር ውስጥና የውጭ ሀገር ባለሃብቶች መሆናቸው ነው የተገለጸው።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)፥ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ምርት ለማምረት በሂደት ያሉ ባለሃብቶች አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴያቸውን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ባለሐብቶቹ በተያዘው በጀት ዓመትና በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ ገደማ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ ለመጀመር ስምምነት የተፈራረሙ ናቸው ተብሏል።

በዚህም ወደ ስራ ከገቡት መካከል ስድስት ኩባንያዎች ምርት ለመጀመር የሚያስችላቸውን ስራዎች በማከናወን ላይ ናቸው።

ወደ ስራ ሲገቡም ከ2000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሆነ የስራ እድልን እንደሚፈጥሩ እንደሚጠበቅ ከኮርፖሬሽኑ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *