በህዳር 24 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ?

የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን እስከ 124 ብር ገዝተው እስከ 127 ብር እየሸጡ ይገኛሉ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው

ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።

ጎህ ቤቶች ባንክ በውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ የሳንቲሞች ጭማሪ በማድረግ ከፍተኛውን ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8705 ብር ገዝቶ በ127.3679 ብር እየሸጠ ይገኛል።

ዳሽን ባንክ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሎ አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።

ኦሮሚያ ባንክ ከሶስት ቀን በፊት ያወጣውን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7099 ብር ገዝቶ በ127.2041 ብር እየሸጠ ይገኛል።

ጸደይ ባንክ የህዳር 24 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ለአንድ ዶላር 124.7010 ብር መግዣ 127.1950 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርቧል።

ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.6425 ብር ገዝቶ በ127.1354 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።

ምንጭ፦ አል.አይን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *