ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በ6 ወራት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ሰበሰበ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ስድስት ወራት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ።

የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣኑ ሠራተኞችና አመራሮች የበጀት ዓመቱ የግማሽ ዓመት አፈጻጸምን ገምግመዋል።

በግምገማው ወቅት እንደተገለጸው ÷ የዚህ በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ገቢ ባለስልጣኑ በ2016 በጀት ዓመት በሙሉ ከሰበሰበው የብር መጠን ጋር የሚመጣጠን ነው።

በዚህም የተቋሙ አጠቃላይ አፈጻጸም 95 በመቶ መሆኑን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል።

በክልል የሚገኙ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ አለመጠናቀቅ እና ተቋሙን የሚለቁ ባለሙያዎች ቁጥር በርካታ መሆን ተቋሙ ካጋጠሙት ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል።

ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣኑ 38ኛውን የአፍሪካ አገራት የመሪዎች ጉባኤን ለመታደም የሚመጡ እንግዶችን በተሳካ መልኩ ለማስተናገድ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ኤም.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *