የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጆችን አፀደቀ።
ምክር ቤቱ አዋጆቹን ያጸደቀው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ሲያካሂድ ነው።
ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ባንክ ሥራ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጆችን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል።
ምክር ቤቱም ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጆቹን አጽድቋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ