የደቡብ አፍሪካ ኤርፖርቶች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል
የኢትዮጵያው ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከአፍሪካ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል
ምርጥ 10 የአፍሪካ ኤርፖርቶች የትኞቹ ናቸው?
ስካይትራክስ የተሰኘው የአቪዮሽን መረጃዎችን በማውጣት የሚታወቀው ተቋም ሪፖርቱን አውጥቷል።
የ2024 ምርጥ የአፍሪካ ኤርፖርቶች ይፋ በተደረጉበት በዚህ ሪፖርት መሰረት ኬፕታወን ኤርፖርት የዓመቱ ምርጥ አንደኛ ተብሎ ተመርጧል።
ደርባን ኪንግ ሻካ እና ጆሀንስበርግ ኤርፖርቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን እንደያዘም ተገልጿል።
የአዲስ አበባው ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከምርጥ 10 የአፍሪካ ኤርፖርት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።
ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከሞሮኮው ማራካሽ በመቀጠል ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
ከአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በመቀጠልም የሩዋንዳው ኪጋሊ እንዲሁም የግብጹ ካይሮ ኤርፖርት 8ኛ እና 9ኛ ደረጃን ይዘዋል።
የጎረቤት ሀገር ኬንያ ናይሮቢ ኤርፖርት ከምርጥ የአፍሪካ ኤርፖርቶች መካከል በ10ኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል።
ምንጭ፦ አል ዐይን