ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና እና የአዘርባጃኑ አላት ነፃ የንግድ ቀጣና በትብብር ለመሥራት ተስማሙ።
ከስምምነት የተደረሰው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የተመራ ልዑክ አላት ነፃ የኢኮኖሚ ዞንን በጎበኙበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።
ጉብኝቱ ለድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ አሠራሮችን ጨምሮ ልምድና ተሞክሮዎች የተቀሰሙበት ነው ተብሏል።
በተጨማሪም በድሬዳዋ እና አላት ነፃ ንግድ ቀጣናዎች መካከል ተቋማዊ ግንኙነት በመፍጠር በትብብር አብሮ ለመሥራት የሚያስችል መደላድል ፈጥሯል መባሉን የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ አመላክቷል።
ምንጭ፦ ኢዜአ