የፓኪስታን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በመድኃኒት እና ጨርቃጨርቅ ዘርፎች ለመሠማራት እንደሚፈልጉ አስታወቁ።
ከ80 በላይ የፓኪስታን ባለሀብቶችን ያካተተ ልዑክ የቂሊንጦ፣ ቦሌ ለሚ እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የሥራ እንቅስቃሴና መሠረተ-ልማቶች ጎብኝቷል።
በጉብኝቱም በመድኃኒት፣ ጨርቃጨርቅ እንዲሁም ሌሎች የቴክኖሎጂ ምርቶችና የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት እንደሚፈልግ ማሳወቁን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ