የባንክ ኦፍ አሜሪካ ፣ጂፒ ሞርጋን እና የሳውዲው አርማኮ መሪዎች የዓለማችን ስኬታማ መሪዎች ተብለዋል።
አሜሪካ፣ ጃፓን ሕንድ እና ደቡብ ኮሪያ ኩባንያ መሪዎች በምርጥ ዓለማችን ስራ አስኪያጅ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል
የዓለማችን ምርጥ 10 የቢዝነስ መሪዎች
ተቋማት ውጤታማ እንዲሆኑ መሪዎች ትልቅ ሃላፊነት ያለባቸው ሲሆን በተለይም ተቋሙ የሚመራበትን የረጅም ጊዜ እቅድ ማውጣት፣ ሰራተኞች በሙሉ ሀይል እና ፍላጎት እንዲሰሩ ማድረግ ዋነኛው ነው
ሲኢኦ መጋዚን ባወጣው መረጃ መሰረት በአሁኑ ወቅት የባንክ ኦፍ አሜሪካ ስራ አስፈጻሚ ብሪያን ሞይኒሀን፣ የጂፒ ሞርጋኑ ጄሚ ዲሞን እና የሳውዲው አርማኮ ኩባንያ ስራ አስፈጻሚ የወቅቱ ምርጥ መሪዎች ብሏቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የኤዞን ሞባይል ስራ አስፈጻሚ ዳረን ውድስ፣ የማይክሮሶፍቱ ሳቲያ ናደላ፣ የአፕሉ ቲም ኩክ እና የቶዮታ ሞተር ስራ አስኪጅ አኪዮ ቶዮዳ ከምርጥ የዓለማችን የቢዝነስ መሪዎች መካከል ተካተዋል።
ምንጭ፦ አል አይን