በመጪው 2024 የኢትዮጵያና ሞሮኮ የቢዝነስ ፎረምን በጋራ ለማዘጋጀት የሚያስችል ስምምነት ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ከሆኑት ናሻ አልዊ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው በኢትዮጵያ የሞሮኮ ባለሀብቶች ሊሳተፉባቸው የሚችሉ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ አማራጮችን ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።
በተጨማሪም በመጪው 2024 የኢትዮጵያ ሞሮኮ የቢዝነስ ፎረምን በጋራ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከኮሚሽሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን