የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊው የኡጋንዳ “ኢኩላ ቱሪዝም ሽልማት” የ2024 ምርጥ የቢዝነስ ክፍል ዘላቂ አገልግሎት ሽልማትን አሸንፏል።
የሽልማት መርሐ ግብሩ በካምፓላ ሸራተን ሆቴል የተካሄደ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኡጋንዳ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገት ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ ሽልማቱ ተበርክቶለታል።
በዚህ ዓመታዊ ሽልማት ለሀገሪቱ ቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት በጎ አሻራ ያሳረፉ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዕውቅና ይሰጣቸዋል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ