ኮርፖሬሽኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተመረቱ ምርቶች ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን በላይ ዶላር መገኘቱን አስታወቀ

ባለፉት አምስት ዓመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተመረቱ ምርቶች ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶችን ችግር ለመፍታት ያለመ የባለድርሻ አካላት ፎረም እየተካሄደ ነው።

ፎረሙ÷ ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚያመርቱ ኢንቨስተሮች የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት፣ እልባት የሚሰጥበት እና አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሆነ ተመላክቷል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እንዳሉት÷ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተመረቱ ምርቶች ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ከ80 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩንም ነው ያስታወቁት።

ኮርፖሬሽኑ አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ ቢሆንም በይበልጥ ውጤታማ ለመሆን የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *