ኢትዮጵያ ዕምቅ የማዕድን ሃብት ስላላት በዘርፉ ትስስር ለመፍጠር እንሠራለን- የፓኪስታን ልዑክ

ኢትዮጵያ ዕምቅ የማዕድን ሃብት ስላላት በዘርፉ ለመሠማራትና ትስስር ለመፍጠር እንሠራለን ሲሉ የፓኪስታን የንግድና የኢንቨስትመንት ልዑክ አባላት ገለጹ።

የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) እና የፓኪስታን የንግድና የኢንቨስትመንት ልዑክ አባላት በአዲስ አበባ ተወያይተዋል።

በዚሁ ወቅትም ለልዑካን ቡድኑ አባላት በማዕድን ዘርፉ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ገለጻ የጠደረገ ሲሆን÷ በዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ መቅረቡንም የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

ውይይቱ በኢትዮጵያ  ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመገንዘብ፣ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር እንደሚያግዝ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር ገልጸዋል።

የፓኪስታን የንግድና የኢንቨስትመንት አባላት በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ዕምቅ የማዕድን ሃብት ያላት በመሆኗ በዘርፉ ለመሠማራትና  ትስስር ለመፍጠር እንሠራለን ብለዋል።

 ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *