የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቻይና ጓንዡ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 ማሳደጉን አስታወቀ።
አየር መንገዱ ከዚህ በፊት የነበረው ሰባት ሳምንታዊ በረራ ላይ ሶስት ሳምንታዊ በረራ መጨመሩን አስታውቋል።
ይህም አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 ከፍ እንደሚያደርገው ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ