አየር መንገዱ ለአፍሪካ አቪዬሽን ልህቀት እያበረከተ ላለው አስተዋፅዖ የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአፍሪካ አቪዬሽን ልህቀት እያበረከተ ላለው አስተዋፅዖ የዕውቅና ሽልማት ከአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን (AFCAC) ተበረከተለት።

አየር መንገዱ በአፍሪካ በርካታ መዳረሻዎች የበረራ አገልግሎት በመስጠት የአፍሪካን አቪዬሽን ኢንደስትሪ በማሳደግ ረገድ ላለው ቁርጠኝነት ነው እውቅናውን ያገኘው።

ሽልማቱ የተበረከተው በኮንጎ ሪፐብሊክ ብራዛቪል ከተማ በተካሄደው 35 ኛው የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን ጉባኤ ላይ ነው።

የአዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ ኤርፖርትም እ.ኤ.አ. ከ2022 እስከ 2024 ዓ.ም ባስተናገደው ከፍተኛ የመንገደኞች ቁጥር ዕውቅና ተሰጥቶታል።

የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን (AFCAC) በአፍሪካ ሕብረት ስር የሚተዳደርና የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ጉዳዮችን የሚከታተል ልዩ ኤጀንሲ ነው።

የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽንበሶስት አመት አንድ ግዜ ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ከአየር መንገዱ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *