የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ሌሎች ተቋማት በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ሃይል ለማስፋፋት ቢያንስ 35 ቢሊየን ዶላር ለመመደብ የሚያስችል ቃል መግባታቸው ተሰምቷል።
በታንዛኒያ ዳሬሰላም ይህን አስመልክቶ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ሃላፊዎች መክረዋል።
ከገንዘቡ ውስጥ ግማሽ ያህሉ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለሌላቸው ማህበረሰቦች አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ለሚያቀርቡ ታዳሽ የኃይል ምንጭ (የፀሃይ ሃይል ሚኒግሪድ) እንደሚሆንም ተጠቁሟል።
ለዚህ የሚሆን ብድርም በአነስተኛ የወለድ መጠን ይገኛልም ነው የተባለው።
የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ፥ ኤሌክትሪክ ከሌለን ሥራ፣ የጤና እንክብካቤና ሌሎች እድሎችን ለማግኘት ከባድ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የመሪዎች ጉባኤው በስድስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ600 ሚሊየን የአፍሪካ ዜጎች መካከል ግማሹን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ ኃይል ለማመንጨት ቃል መግባቱን የዘገበው ኒው ዮርክ ታይምስ ነው።
ምንጭ፦ ኤፍ.ኤም.ሲ