በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ልማት ትብብርን ማጠናከር ላይ ያተኮረ መድረክ ተካሄደ

የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የኢኮኖሚ ልማት ትብብርን ማጠናከር ላይ ያተኮረ የ21ኛው የአፍሪካ ቀንድ የሚኒስትሮች ኢኒሼቲቭ የውይይት መድረክ በኬኒያ ናይሮቢ ተካሂዷል።

መድረኩ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የ2024 ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የተካሄደው።

መድረኩ በኢኒሼቲቩ የስራ አፈጻጸም እንዲሁም ፍኖተ ካርታ፣ሀገር በቀል የሆኑ የኢኮኖሚ ልማት ፕሮጀክቶች ትግበራ፣ ባለቤትነትና አመራር ሰጪነት አስፈላጊነት ዙሪያ መክሯል።

በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ልዩነት እና ሌሎች የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመፍታት የኢኮኖሚ ልማት ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከሩን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

መድረኩን የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ዋና መሪነትና የአፍሪካ ልማት ባንክ ማሪያ-ላውሬ በምክትል መሪነት አስተባብረውታል ።

በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በኬንያ ናይሮቢ “የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን እና ዓለም አቀፍ የፋይናንሺያል አርክቴክቸር ማሻሻያ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ መሆኑ ይታወቃል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *