በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና በሥራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የተመራ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በአዳማ ከተማ የጎጆ ኢንዱስትሪ ልማትን እየጎበኘ ይገኛል።
በአዳማ ከተማ ከ5 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በላይ 35 ኢንተርፕራይዞች በጎጆ ኢንዱስትሪ ልማት ተሰማርተው እየሠሩ እንደሚገኙ እና በዚህም ከ300 በላይ የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተገልጿል።
የጎጆ ኢንዱስትሪ ልማት የዕደ ጥበብ ሙያን ወደ ሥራ ዕድል አማራጭ ለማስገባት ሚናው የጎላ መሆኑም ተመላክቷል።
በጎጆ ኢንዱስትሪው ጨርቃጨርቅ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ የአዮዲን ጨው፣ ፍሳሽ ሳሙና እና ሌሎች ምርቶች እየተመረቱ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ ገልጸዋል።
በአዳማ ከተማ ባለፋት ስድስት ወራት የጎጆ ኢንዱስትሪን ጨምሮ በተለያዩ የሥራ መስኮች ለ19 ሺህ 180 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩንም አቶ ኃይሉ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።