በባንኩ የዲጂታል አማራጮች የ5 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር ዝውውር ተፈጸመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ስድስት ወራት በዲጂታል አማራጮች የ5 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር ዝውውር መፈፀሙን አስታወቀ።

የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ ዲቪዥን መርቻንትና ኤጀንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር ብሌን ኃይለሚካኤል እንዳሉት÷ባንኩ 30 ሚሊየን የሲቢኢ ብርና 9 ሚሊየን የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች አሉት።

በተጨማሪም 21 ሚሊየን የካርድ ባንኪንግ እና 4 ሺህ በላይ የፖስ ማሽን ተጠቃሚዎች እንዳሉት ነው የገለጹት።

በእነዚህ የዲጂታል አማራጮችም ባለፉት ስድስት ወራት 910 ሚሊየን ግብይቶች መከናወናቸውን አስረድተዋል።

በዚህም የ5 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር ዝውውር የተፈጸመ ሲሆን፥ አሁን ላይም 79 በመቶ የባንኩ የገንዘብ ዝውውር ሥራ በዲጂታል አማራጮች እንደሚካናወን ለኢዜአ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *