የካቲት 27/2015ዓ.ም(ኢ.ሚ) ላለፉት ሁለት ዓመታት በኮቪድ እና በአሜሪካ የቀረጥ ነጻ ዕድል መሰረዝ ምክንያት ስራ ያቆመውን የሁዋጃን ላይት ኢንዱስትሪ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት የሚረዳ ውይይት ተካሄዷል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከሁዋጃን ላይት ኢንዱስትሪ ባለቤት ሁዋሮንግ ዣንግ ጋር ኢንዱስትሪውን ሙሉ በሙሉ ወደስራ ለማስገባት በነበራቸው ውይይት ላይ በቅርቡ የገበያያ ትስስር ተፈጠሮለት ወደ ማምረት ስራው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የሃገራችን ጫማ አምራች ኢንዱስትሪ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን እና አዳዲስ የቻይና ባለሀብቶችን ለመሳብ ጥረት እንደሚያደርጉ የኢንዱስትሪው ባለቤት ተናግረዋል፡፡
ኢንዱስትሪው ወደ ስራ እንዲገባ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡