በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እና በስዊድን ማዕከላዊ ባንክ (ሪክስ ባንክ) ገዥ መካከል የትብብር ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል።
የትብብር ስምምነቱ፣ የቴክኒክ፣ የምርምር፣ የኮሙኒኬሽን እና ዲጂታይዜሽን ትብብሮችን እንደሚያካትት መገለጹን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመላክታል።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ፣ የብሔራዊ ባንክ ማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ወደነበረበት ለመመለስ እና መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን እንደገና ለማነቃቃት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ስታንዳርድ ባንክ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ከበርካታ የውጭ ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ