ጀርመን ሦስተኛዋ የዓለም ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ደረጃን ከጃፓን ተረከበች።
ይህን ተከትሎም በዓለም ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት በቅደም ተከተል አሜሪካ ፣ ቻይና እና ጀርመን ሆነዋል።
ጃፓን ደግሞ ከዚህ በፊት ከነበረችበት 3ኛ ደረጃ በጀርመን ተቀድማ አራተኛዋ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ መሆኗን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል።
የጃፓን ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ባለፈው ዓመት 4 ነጥብ 2 ትሪሊየን ዶላር የነበረ ሲሆን ፥ በአንጻሩ የጀርመን 4 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር መድረሱ ተመላክቷል።
የጃፓን መገበያያ ገንዘብ “የን” ምንዛሬ ዝቅ ማለት ጀርመን ሦስተኛዋ የዓለም ባለግዙፍ ኢኮኖሚ እንድትሆን ትልቅ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል።
ጃፓን በቻይና እስከተነጠቀችበት የፈረንጆቹ 2010 ድረስ የዓለም ሁለተኛዋ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ እንደነበረችም ዘገባው አስታውሷል።