
በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተካሄደው 33ኛው የአፍሪካ፣ እስያና ዓረብ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የተሳተፉ የጃፓን ባለሀብቶች ለቅድመ ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ገለጹ።
ባለሀብቶቹ በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ማረጋገጣቸውን የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ አመላክቷል።
በዚህም በኢትዮጵያ በማምረቻ፣ በንግድ፣ ሎጂስቲክ እና በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ነው የተገለጸው።
በቅርቡም ለቅድመ ኢንቨስትመንት ጥናት እና ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ተጠቅሷል።
ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ ሥራችንን ለመሥራት የሚያስችል የሰለጠነ ወጣት የሰው ኃይል፣ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ ሰፊ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ገበያ መዳረሻ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገነቡ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ነጻ ንግድ ቀጣና መኖራቸውን በውይይቱ ላይ ተረድተናል ብለዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢንቨስትመንት ሂደቱን ቀልጣፋ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ባለሃብቶቹ ውጤታማ የሚሆኑበት መንገድ እንደሚመቻች ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ኤም.ሲ